png-logo-white   GREAT ETHIOPIAN RUN

English Arabic Chinese (Simplified) French German Japanese Norwegian Russian Spanish

የማራቶን እና 3000ሜ. መሰናክል የሜዳልያ ድሎቻችን ይቀጥሉ ይሆን?
ቀጣዩ ዘገባ በሪዮ ኦሊምፒክ በመካከለኛ ርቀት፣ በ3000ሜ. መሰናክል እና በማራቶን በሁለቱም ፆታዎች እንዲሁም በ20 ኪ.ሜ. እርምጃ ሴቶች የኢትዮጵያ ተወካዮች በሆኑት አትሌቶች ዙሪያ የተወሰነ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይሞክራል፡፡                  

መካከለኛ ርቀት
በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በነበሯት የኦሊምፒክ ተሳትፎዎች ምንም አይነት ሜዳልያን ያላስመዘገበችበት ቢሆንም በሪዮ ኦሊምፒክ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የመካከለኛ ርቀት የሜዳልያ ድል ሊመዘገብ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
በወንዶች 800 ሜ. ከአራት ዓመት በኋላም ዳግም ብቸኛው የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ለመቅረብ የበቃው መሐመድ አማን ከለንደን ኦሊምፒክ በኋላ በ2013 ሞስኮ ላይ የዓለም ሻምፒዮን፣ በ2014 ሶፖት ላይ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን አንዲሁም በሞሮኮ ማራካሽ በተካሄደው የ2014 ኮንቲኔንታል ካፕ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ቢሆንም የ2015 እና 2016 ውድድር ዓመቶች የውድድር ተሳትፎው ተደጋጋሚ የአቋም መዋዠቆች የታየበት ነበር፡፡ ሌሎች ሁለት አትሌቶችን ማሳተፍ ይቻል የነበረ ቢሆንም በርቀቱ ለመሳተፍ የሚያስችለውን ሰዓት የሚያሟሉ ሌሎች አትሌቶችን ማፍራት አለመቻሉ አሁንም ትልቅ ክፍተት ሆኖ መቀጠሉን ያመላክታል፡፡


በሴቶች 800 ሜትር ከአራት ዓመት በፊት ብቸኛ ተወካይ ሆና የቀረበችው ፋንቱ ሜግሶ ወደስፍራው ብታቀናም ከጉዳት ጋር በተያያዘ ሳትወዳደር መመለሷ የሚታወቅ ሲሆን በሪዮ በሴቶቹ በኩል ሰዓቱን አሟልተው መወዳደር የሚችሉ ሶስት አትሌቶችን ለማቅረብ መቻሉ እሰየው የሚያሰኝ ነው፡፡ ሀብታም አለሙ፣ ጉዳፍ ፀጋዬ እና ትዕግስት አሰፋ በሴቶች 800ሜ. የወቅቱ ድንቅ ብቃት ባለቤት የሆነችው ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሴመንያ እና ኬንያውያን አቻዎቻቸው ብርቱ ተፎካካሪ መሆን እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ በተለይ ዘንድሮ በተደጋጋሚ ርቀቱን ከሁለት ደቂቃ በታች በሆነ ሰዓት መጨረስ የቻለችው ሀብታም አለሙ ምናልባትም ሳትታሰብ ከሜዳልያ አሸናፊዎች ተርታ ልትገባ የምትችልበት አቅም እንዳላት በዘንድሮው የዳይመንድ ሊግ መክፈቻ ውድድር ዶሀ ላይ ከሴመንያ ጋር ተናንቃ ሁለተኛ ሆና ባጠናቀቀችበት አጋጣሚ አመላክታለች፡፡
Rio Olympic 1500m Men teamየወንዶች 1500ሜ. ተወካዮቻችን በሙሉ በለንደን 2012 ላይም የነበሩት አማን ወጤ፣ መኮንን ገ/መድህን እና ዳዊት ወልዴ ሲሆኑ ከለንደኑ የተሻለ ተፎካካሪ ሆነው እንደሚቀርቡ ተስፋ ይደረጋል፡፡ የዚህ ርቀት የወርቅ ሜዳልያ ከኬንያዊው አስቤል ኪፕሮፕ እንደማያልፍ ሰፊ ግምት ቢኖርም አልጄሪያዊው ቶፊቅ ማክሉፊ ለንደን ላይ እንዳደረገው ያልተጠበቀ አሸናፊን ልናይ የምንችልበት ዕድልም ሙሉ በሙሉ ዝግ አይደለም፡፡
የርቀቱ የዓለም ሪኮርድ ባለቤት እና የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮን ገንዘቤ ዲባባ ከዳዊት ስዩም እና በሱ ሳዶ ጋር ኢትዮጵያን የምትወክልበት የሴቶች 1500ሜ. በመካከለኛ ርቀት የኦሊምፒክ ሜዳልያን ለመጀመሪያ ግዜ እንደምናስመዘግብ ተስፋ የምናደርግበት ውድድር ነው፡፡ ከአበረታች መድኃኒት ጋር በተያያዘ በግል አሰልጣኟ ላይ የቀረበው ክስ በገንዘቤ ላይ ስነልቦናዊ አለመረጋጋትን ሳይፈጥርባት እንዳልቀረ የሚታመን ሲሆን የርቀቱ ተመራጭ መሆኗን ያረጋገጠችበትን ሰዓት ለማሟላት የበቃችውም ሚኒማ ለማሟላት የተቀመጠው የግዜ ቀነ ገደብ ሊያልቅ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ነበር፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በለንደን የርቀቱን የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ በማድረግ ላይ እያለች ባጋጠማት ጉዳት ምክንያት ወደግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ሳትችል የቀረችው ገንዘቤ በሪዮ ኦሊምፒክ የ1500ሜ. ውድድር የለንደን መጥፎ ገጠመኟን የምትረሳበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕዬጎን እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድ ተወካይ ሲፋን ሀሰን የገንዘቤ የቅርብ ተቀናቃኞች እንደሚሆኑም ይገመታል፡፡


ማራቶን
Ethiopian Woman Marathon Team for Rio 2016 1ማራቶን ከዛሬ 56 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ አትሌቲክስ የኦሊምፒክ ድል ገድል በአበበ ቢቂላ የተጀመረበት ውድድር እንደመሆኑ ሌላኛው በጉጉት የሚጠበቅ እና ከ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ቀጥሎ ኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ሜዳልያዎችን (6 የወርቅ እና 3 የነሐስ) በብዛት ያገኘችበት የውድድር አይነት ነው፡፡ በሴቶች ከረጅም ግዜ ቆይታ (ከአትላንታ 1996 ወዲህ) በለንደን 2012 የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳልያን ማሳካት የቻልንበት ማራቶን በወንዶች ከሲድኒ 2000 ኦሊምፒክ ወዲህ ድልን የምንናፍቅበት እንደሆነ አለ፡፡ የኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ሁልግዜም የሚጠበቁ አትሌቶች የሚያሸንፉበት ባለመሆኑ በሪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን ለማሸነፍ የሚኖራቸው ዕድልም ከሌሎች ብርቱ ተፎካካሪዎቻቸው የሚተናነስ ይሆናል ተብሎ አይታመንም፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከታዩት ሁነቶች አኳያ ሴት ተወዳዳሪዎቻችን የተሻለ ስኬትን ሊጎናጸፉ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡ በወንዶቹ በኩል በተለይ የኬንያውያኑ ተወዳዳሪዎች ጥንካሬ በልበ ሙሉነት የወርቅ ሜዳልያውን እናሸንፋለን ብሎ ለመናገር የሚያስደፍር አይደለም፡፡ ሆኖም በወንዶች ለሚ ብርሀኑ፣ ተስፋዬ አበራ እና ፈይሳ ሌሊሳ በሴቶች ትግስት ቱፋ፣ ማሬ ዲባባ እና ትርፊ ፀጋዬ የተካተቱበት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ማራቶን ቡድን ከኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ኤርትራውያን ተፎካካሪዎቹ ጋር ብርቱ ትንቅንቅ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ 
በለንደን ኦሊምፒክ የወንዶች ማራቶን ፉክክር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሶስቱም አትሌቶች አቋርጠው መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን በሴቶች ቲኪ ገላና የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ፣ የሪዮ ኦሊምፒክ ቡድን ውስጥም ለመካተት የበቃችው የቤይጂንግ ዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ ማሬ ዲባባ 23ኛ እንዲሁም አሰለፈች መርጊያ 42ኛ ሆነው ማጠናቀቃቸውም ይታወሳል፡፡

3000ሜ. መሰናክል
3000ሜ. መሰናክል በሁለቱም ፆታዎች አንድ አንድ ግዜ (እሸቱ ቱራ በ1980 የነሐስ እና ሶፊያ አሰፋ በ2012 የነሐስ*) የኦሊምፒክ ሜዳልያን የተቋደስንበት የውድድር አይነት ሲሆን በሪዮ ኦሊምፒክም በሁለቱም ፆታዎች ሙሉ ውክልና ይኖረናል፡፡ በሴቶች ከሶስት ዓመት በፊት የወከሉን ሶስቱም አትሌቶች (የነሐስ ሜዳልያ አሸናፊዋ ሶፊያ አሰፋ፣ ሕይወት አያሌው እና እቴነሽ ዲሮ) ከኬንያውያን አቻዎቻቸው ጋር የሚፎካከሩ ሲሆን በወንዶች ታፈሰ ሰቦቃ፣ የአፍሪካ ሻምፒዮኑ ጫላ በዩ እና ኃ/ማርያም አማረ ይሳተፋሉ፡፡ በውድድር ሜዳ ላይ ያልተጠበቁ አሸናፊዎች ብቅ ሊሉ የሚችሉበት ዕድል ያለ ቢሆንም በ3000ሜ. መሰናክል የወንዶች ፉክክር ግን የኬንያውያን የበላይነት የማይደፈር አይነት መሆኑን በተለያዩ ውድድሮች ላይ ያየነው ከመሆኑ አንፃር አሸናፊነቱ ከእነርሱ እንደማይዘል መገመቱ ስህተት አይሆንም፡፡ በሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለይም ሶፊያ አሰፋ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ካሳየችው ብቃት አንፃር የሜዳልያ ደረጃ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ይገመታል፡፡ ኬንያዊቷ የዓለም ሻምፒዮን ሀይቪን ኪገን እና ትውልደ ኬንያዊቷ የባሕሬይን ተወካይ ሩት ጄቤት በርቀቱ የአሸናፊነቱን የቅድሚያ ግምት የሚያገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡    
    
* የሶፊያ አሰፋ የለንደን ኦሊምፒክ የነሐስ ሜዳልያ በዶፒንግ ምክንያት የሩሲያዊቷ የውድድሩ አሸናፊ ዩሊያ ዛሪፖቫ ውጤት መሰረዙን ተከትሎ ወደ ብር ሜዳልያ እንደሚያድግ ቢገለፅም ይህ ዘገባ እስከተሰራበት ሰዓት ድረስ በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ይፋዊ ማረጋገጫ አልሰጠበትም፡፡     

የሴቶች 20 ኪ.ሜ. እርምጃ
ከአራት ዓመት በፊት በለንደን ኦሊምፒክ ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊው በረከት ደስታ በወንዶች 400ሜ. ያልተጠበቀ ተሳትፎን ማሳካት ችሎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በሪዮ ኦሊምፒክ ደግሞ ኢትዮጵያ በሌላ ያልተጠበቀ ርቀት (20 ኪ.ሜ. እርምጃ) በሁለት እንስት አትሌቶች ትወከላለች፡፡ በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ ደርባን በተካሄደው 20ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የራሷ ምርጥ በሆነ 1፡31.58 ሰዓት የብር ሜዳልያ በማሸነፍ ጭምር ሚኒማ ያመጣችው የኋልዬ በለጠ እና ባለፈው ግንቦት ወር በጣልያን ሮም በተካሄደው የአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ የዓለም እርምጃ ሻምፒዮና ላይ የርቀቱን ሚኒማ ያሟላችው አስካለ ጢክሳ ለመጀመሪያ ግዜ በኦሊምፒክ መድረክ የኢትዮጵያ የእርምጃ ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ፡፡

Share

ተጨማሪ ዜናዎች

አልማዝ አያና በሪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የዓለም እና የኦሊምፒክ ሪኮርድ በመስበር ጭምር የወርቅ ሜዳልያ አሸነፈች ፤ ጥሩነሽ ዲባባም የነሐስ ሜዳልያ ድልን አሳክታለች

የሪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ፉክክር ከተጀመረ ከስምንት ቀን በኋላ (ሐምሌ 6/2008) መካሄድ በጀመረው የአትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የርቀቱን የዓለም ሪኮርድ በመስበር ጭምር በአትሌቲክስ የመጀመሪያዋ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች፡፡ ከዚህ በፊት በርቀቱ የቤይጂንግ እና ለንደን ኦሊምፒኮች የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት የነበረችው ጥሩነሽ ዲባባም በአራተኛ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ከአልማዝ አያና እና ኬንያዊቷ ቪቪያን ቼሪዮት ቀጥላ በሶስተኛነት በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳልያ አሸናፊ ሆናለች፡፡

ተጀምሮ እስኪያልቅ ኬንያዊቷ የአፍሪካ ሻምፒዮን አሊስ አፕሮት እና አልማዝ አያና ተቀባብለው የመሩበት ሴቶች 10 ሺህ ሜ. ፉክክር ከተጀመረ ከሶስተኛው ዙር አንስቶ በሁለቱ ፊት መሪዎች አስገዳጅነት ስምንት አትሌቶች - አፕሮት (ኬንያ)፣ አልማዝ (ኢትዮጵያ)፣ ቼሪዮት (ኬንያ)፣ ያስሚን ካን (ቱርክ)፣ ጥሩነሽ (ኢትዮጵያ)፣ ቤትሲ (ኬንያ)፣ ገለቴ (ኢትዮጵያ) እና ሀድል (ዩ.ኤስ.ኤ) - በቅደም ተከተል ተነጥለው የወጡበት የነበረ ሲሆን 4800ሜ. ላይ ሲደርሱ ገለቴ እና ሞሊ ሀድል ወደኋላ ቀርተዋል፡፡ 5200ሜ. ከሸፈኑ በኋላ ውድድሩን የመምራቱን ኃላፊነት የተረከበችው አልማዝ ፍጥነቷን በመጨመር ስትወጣ ኬንያዊቷ ቼሪዮት የተከተላቻት ቢሆንም በቀጣዮቹ ዙሮች እየጨመረ የመጣውን የአልማዝ ፍጥነት መቋቋም ሳትችል ቀርታ ተሸንፋለች፡፡ በአልማዝ እና ቼሪዮት መካከል የነበረው ልዩነት በመጨረሻዎቹ ስምንት ዙሮች እየሰፋ ሄዶ አልማዝ 29 ደቂቃ ከ17.45 ሰከንድ በሆነ አዲስ የዓለም እና የኦሊምፒክ ሪኮርድ ሰዓት በሪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ውድድር የመጀመሪያዋ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች፡፡ ከውድድሩ ጥቂት ወራት ቀደም ብላ በሰጠችው አስተያየት አልማዝንም ቢሆን እንደማትፈራ ተናግራ የነበረችው ኬንያዊቷ ቼሪዮት በዘጠና ሜትር ያህል ልዩነት ተቀድማ የራሷ ምርጥ እና የኬንያ ሪኮርድ በሆነ 29:32.53 ሰዓት ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ 

Read more...

በሪዮ ደ ጃኔይሮ በመካከለኛ ርቀት የመጀመሪያውን የኦሊምፒክ ሜዳልያ እንደምናስመዘግብ ይጠበቃል

የማራቶን እና 3000ሜ. መሰናክል የሜዳልያ ድሎቻችን ይቀጥሉ ይሆን?
ቀጣዩ ዘገባ በሪዮ ኦሊምፒክ በመካከለኛ ርቀት፣ በ3000ሜ. መሰናክል እና በማራቶን በሁለቱም ፆታዎች እንዲሁም በ20 ኪ.ሜ. እርምጃ ሴቶች የኢትዮጵያ ተወካዮች በሆኑት አትሌቶች ዙሪያ የተወሰነ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይሞክራል፡፡                  

መካከለኛ ርቀት
በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በነበሯት የኦሊምፒክ ተሳትፎዎች ምንም አይነት ሜዳልያን ያላስመዘገበችበት ቢሆንም በሪዮ ኦሊምፒክ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የመካከለኛ ርቀት የሜዳልያ ድል ሊመዘገብ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
በወንዶች 800 ሜ. ከአራት ዓመት በኋላም ዳግም ብቸኛው የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ለመቅረብ የበቃው መሐመድ አማን ከለንደን ኦሊምፒክ በኋላ በ2013 ሞስኮ ላይ የዓለም ሻምፒዮን፣ በ2014 ሶፖት ላይ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን አንዲሁም በሞሮኮ ማራካሽ በተካሄደው የ2014 ኮንቲኔንታል ካፕ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ቢሆንም የ2015 እና 2016 ውድድር ዓመቶች የውድድር ተሳትፎው ተደጋጋሚ የአቋም መዋዠቆች የታየበት ነበር፡፡ ሌሎች ሁለት አትሌቶችን ማሳተፍ ይቻል የነበረ ቢሆንም በርቀቱ ለመሳተፍ የሚያስችለውን ሰዓት የሚያሟሉ ሌሎች አትሌቶችን ማፍራት አለመቻሉ አሁንም ትልቅ ክፍተት ሆኖ መቀጠሉን ያመላክታል፡፡

Read more...

በሪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክሱ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ቀን ውሎዎች ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሁለት የነሐስ ሜዳልያዎችን አግኝታለች

ታምራት ቶላ በወንዶች 10000 ሜ. ማሬ ዲባባ በሴቶች ማራቶን ሜዳሊያዎቹን አስገኝተዋል


ታምራት ቶላ ነሐስ ያገኘበት የወንዶች 10000ሜ. ፍፃሜ

በሪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሁለተኛ ቀን ውሎ ተጠባቂ ከነበሩት የፍፃሜ ፉክክሮች አንዱ በሆነው የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን አትሌቶች ላለፉት አራት ዓመታት የርቀቱ ንጉስ ሆኖ የቆየውን ትውልደ ሶማሊያዊ የእንግሊዝ አትሌት ሞ ፋራህ ዳግም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ሞ ፋራህ በሪዮው ድሉ በኦሊምፒክ ውድድር በተከታታይ ሁለተኛ የ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድልን በመቀዳጀቱ በታሪክ መዝገብ ላይ ስሙ ከቀደሙት ታላላቅ አትሌቶች ጎራ እንዲመደብ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ተወዳዳሪዎች እርሱን ለማሸነፍ ምን አይነት ታክቲክ ይጠቀሙ ይሆን የሚለው ከውድድሩ በፊት የብዙዎች ጥያቄ የነበረ ቢሆንም በለንደን ኦሊምፒክ እንዲሁም በሞስኮ እና ቤይጂንግ የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ ከተመለከትነው ብዙም የተለየ ነገር ሳይታይ ሞ ፋራህ ዳግም በመጨረሻው ዙር የአጨራረስ ብቃቱ ከተፎካካሪዎቹ ልቆ በመገኘት ለማሸነፍ በቅቷል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ታምራት ቶላ እና ይግረም ደመላሽ እንዲሁም ሶስቱ ኬንያውያን ውድድሩን እየተፈራረቁ በመምራት ለማፍጠን ያደረጓቸው ጥረቶች ስኬታማ መሆን አልቻሉም፡፡ ውድድሩ 15 ዙር እየቀረው የመውደቅ አደጋ አጋጥሞት የነበረው ሞ ፋራህ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት በፍጥነት ተነስቶ መቀጠል የቻለ ሲሆን በመጨረሻው ዙር ከኬንያዊው ፖል ታኑዪ ጋር በነበረው ፉክርም 100ሜ. ሲቀር አልፎት በመሄድ በ27 ደቂቃ ከ05.17 ሰከንድ አንደኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ፖል ታኑዪ በ27፡05.64 ሁለተኛ ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ በ27፡06.26 ሶስተኛ በመሆን የብር እና የነሐስ ሜዳልያዎችን አሸንፈዋል፡፡ በርቀቱ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት የሆነው ኢትዮጵያዊው

Read more...